The Airline: Ethiopian Airlines




Ethiopian Airlines (Amharic: የኢትዮጵያ አየር መንገድ; የኢትዮጵያ? in short), formerly Ethiopian Air Lines, often referred to as simply Ethiopian, is an airline headquartered on the grounds of Bole International Airport in Addis Ababa, Ethiopia. It serves as the country's flag carrier, and is wholly owned by the Government of Ethiopia. From its hub in Bole International Airport the airline serves a network of 62 international destinations and 16 domestic ones. The carrier flies to more destinations in Africa than any other airline. Likewise, it is one of the few Sub-Saharan profitable airlines, as well as one the fastest growing airlines in the industry. The airline's cargo division has been awarded The African Cargo Airline of the Year in early 2011.
As of December 2011 the airline is a Star Alliance member. Ethiopian is also a member of the International Air Transport Association, and of the African Airlines Association (AFRAA) since 1968.







Amharic description below:


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ የሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አየር መንገድ ድርጅት ነው። አየር መንገዱ ከቀድሞው ትራንስ ወርልድ ኤየርዌይስ/ Transworld Airways (TWA) ጋር በጋራ የተመሠረተ ሲሆን አስተዳደሩ በአሜሪካኖች እጅ ነበር፤ ድርጅቱ ታኅሣሥ ፳፩ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ተመሥርቶ ለመጀሜሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ በረራውን መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ከአዲስ አበባ ተነሥቶ ካይሮ ድረስ አከናወነ።

አየር መንገዱ ሲመሠረት ከአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የተገዙና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ያገለገሉ አምስት ዲ.ሲ. ፫ (DC 3-C47) አውሮፕላኖች ነበሩት። በዓለም ዙሪያ በአፍሪካ፤ በእስያ፤ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ክፍለ አህጉራት ወደ ፶ የመንገደኛና የጭነት አገልግሎት ሲሰጥ፤ በሀገር ውስጥ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ፲፮ መድረሻዎችን ያገለግላል። ዋና የጣቢያው ማዕከል በአዲስ አበባ የሚገኘው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የራሱ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ሲኖረው የግል አብራሪ እና የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ በመስጠት የሀገር ልጆችንም ሆነ የውጭ ዜጎችን በማሰልጠን እስከ አርባ ዓመት ልምድ አለው። እንዲሁም ለብዙ የአፍሪካ ሀገር ብሔራዊ አየር መንገዶችና የግል አውሮፕላኖች የጥገና አገልግሎት ይሰጣል።
አየር መንገዱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥት የተያዘ የኢትዮጵያውያን ሀብት ሲሆን፤ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ለሽያጭ እና ለግዢ እንዲሁም ለብድር አመቺ እንዲሆን ተብሎ በአየር መንገዱ ሙሉ ቁጥጥር ሥር በኬይማን ደሴቶች የተመሠረተ ድርጅት ባለቤት ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ለመንገደኞች አገልግሎት አዲሱንና ዘመናዊውን የቦይንግ ፯፻፹፯(Boeing 787) ድሪምላይነር አውሮፕላን በማዘዝና ጥቅም ላይ በማዋል ከአፍሪካ የመጀመሪያው አየር መንገድ ሊሆን ነው። የታዘዙትን አሥር ቦይንግ ፯፻፹፯ ድሪምላይነር (Boeing 787 Dreamliner) አውሮፕላኖች እ.አ.አ. በ2009 መጨረሻ ላይ እንደሚረከብና ጥቅም ላይ እንደሚያውል ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ አየር መንገዱ 8 ቕ400 አውሮፕላኖች ከቦምባርዲየር (Bombardier ለሀገር ውስጥ መንገደኞት አገልግሎት አዟል።

በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ዓለማየሁ በቀለ በላይነህ፣ ማትያስ ሰሎሞን በላይ እና ሱልጣን አሊ ሁሴን የተባሉ ሦስት ኢትዮጵያውያን፣ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በናይሮቢ በኩል ወደ ቦምቤይ በረራ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በረራ ቁ. ፱፻፷፩ በዓየር ላይ ጠለፉ። በጠላፊዎቹም ትእዛዝ ወደ አውስትራሊያ ሲያመራ ነዳጅ በመጨረሱ ምክንያት በረራው በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ወደምትገኘው የቆሞሮስ ደሴት ተጠግቶ ከደሴቷ ግማሽ ኪሎሜትር ውቅያኖሱ ላይ ሊያርፍ ሲሞክር የዓየር ተሽከርካሪው ተሰባብሮ ፈነዳ። ከመንገደኖቹም ውስጥ፣ ጠላፊዎቹን ጨምሮ መቶ ሃያ ሦሥት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ከሞቱት መንገደኞች አንዱ፣ ኬንያዊው የፎቶ-ጋዜጠኛ ሞሐመድ አሚን ነበር።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ፬፻፱ ጥር ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባልታወቀ አደጋ ምክንያት በሜድትራኒያን ባሕር ላይ ውድቆ የሰመጠ በረራ ነበር።

0 comments:

Post a Comment

Twitter Delicious Facebook Digg Stumbleupon Favorites More

 
Design by Free WordPress Themes | Bloggerized by Lasantha - Premium Blogger Themes | Blogger Templates